Aller au contenu principal

page search

Bibliothèque በኢትዮጵያ ኃላፊነት የተሞላበት የማህበራዊና አካባቢ የስነ ምግባር ደንብ

በኢትዮጵያ ኃላፊነት የተሞላበት የማህበራዊና አካባቢ የስነ ምግባር ደንብ

በኢትዮጵያ ኃላፊነት የተሞላበት የማህበራዊና አካባቢ የስነ ምግባር ደንብ

Resource information

Date of publication
Novembre 2018
Resource Language
Pages
54

በኢትዮጵያ ኃላፊነት የተሞላበት የግብርና ኢንቨስትመንት ዕውን ለማድረግ የሚያስችል የማህበራዊና አካባቢ የስነ ምግባር ደንብ የተዘጋጀው የግብርና ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ሁሉን አቀፍ ፣ዘላቂ ፣ ግልጽነት የሰፈነባቸው እና ሰብአዊ መብቶችን የሚያከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይችሉ ዘንድ ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ የስነ ምግባር ደንብ ሰነድ ነው ፡፡ ይህ ሰነድ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸርና ግብርና ኢንቨስትመንት ባለስልጣን የግብርና ኢንቨስትመንት ልማት በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ መመሪያዎችን ለማዘጋጀት ባሳየው ቁርጠኝነት ምክንያት ነው፡፡

የማህበራዊና አካባቢ የስነምግባር ደንብ በርካታ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች የሚያደርጉትን ጥረት ያጣምራል እንዲሁም የራሱን ግብአት በመጨመር ያዳብራል፡፡ እነዚህም አለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች ያዘጋጇቸው ሰነዶች ፦ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ እና ሃላፊነት የተሞላ የመሬት፣ የአሳ እና የደን ሀብቶች አስተዳደር (በብሄራዊ የምግብ ዋስትና ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ) መርሆዎች (VGGT) ፣ በአፍሪካ የሚደረጉ መጠነ ሰፊ መሬት ላይ የተመሰረቱ ኢንቨስትመንቶች መመሪያ መርሆዎች (LSLBI) ፣ በግብርና እና በምግብ ስርአቶች ላይ የሚደረግ በኃላፊነት የተሞላ ኢንቨስትመንት መርሆዎች (RAI) እና መሬት ላይ ለተመሰረተ የአፍሪካ ግብርና ኢንቨስትመንት መዋቅራዊ ትንታኔ ሲሆኑ የእነዚህን እና መሰል እንቅስቃሴዎችን ዋና ዋና መርሆዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ፖሊሲዎች እና የህግ ማዕቀፎች ጋር በማጣጣም ይሰራል የማህበራዊና አካባቢ የስነምግባር ደንብ ፡፡

ስነ ምግባር ደንቡ ከላይ የተጠቀሱትን ዋቢ ሰነዶች ለመተካት አይደለም የተዘጋጀው፤ ይልቁንስ ከእኒዚህ መመሪያዎች ውስጥ ጠቃሚ መርሆዎች እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማጥለል እና በማዘጋጀት የኩባንያ ሰራተኞች፣ የፈፃሚ አካላት ሃላፊዎች፣ እና ሌሎች የግሉ ዘርፍ ባለሙያዎች በእርሻ ላይ የሚያደርጉት ኢንቨስትመነት ኢንቨስትመንቱ በሚፈጀው አጠቃለይ ጊዜ የአካባቢያዊ እና ማህበራዊ ሃለፊነታቸውን ዝቅተኛ መስፈርቶች የሚያሟሉ አፈፃፀሞችን ማሳየታቸውን ወይም ከሚጠበቀውም በላይ ማሳካታቸውን ለመገምገም የሚጠቀሙበት ሲሆን የሚጠበቅባቸውን ሳያሟሉ ከቀሩም ችግሩን እንዴት መፍታት እንደሚችሉ ይጠቁማቸዋል፡፡

Share on RLBI navigator
NO