Aller au contenu principal

page search

Bibliothèque የመሬት ይዞታ መብት በኃላፊነት ማስተዳደርን የተመለከተ የኢንቬስተሮች ሙያዊ መምሪያ

የመሬት ይዞታ መብት በኃላፊነት ማስተዳደርን የተመለከተ የኢንቬስተሮች ሙያዊ መምሪያ

የመሬት ይዞታ መብት በኃላፊነት ማስተዳደርን የተመለከተ የኢንቬስተሮች ሙያዊ መምሪያ

Resource information

Date of publication
Novembre 2016
Resource Language
ISBN / Resource ID
ISBN 978-92-5-131436-4
Pages
88

በግብርና ስራ ላይ የሚውል ኢንቨስትመንት በምግብ ራስን አለመቻልንና ድህነትን ለመቀነስ እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በታዳጊ አገሮች ውስጥ የእርሻ ቦታ ተፈላጊነት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ በዚህ አኳያ መሬት አጉዋጊ መስህብነት ያለው ቋሚ ንብረት ተደርጐ ይወሰዳል፡፡ በማህበራዊ ዘርፍ ረገድ በመሬት ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ቅይጥ ውጤቶችን አምጥተዋል፡፡ እንደነዚህ ያሉ ኢንቨስትመንቶች የአንዱን አካባቢ ማህበረሰቦች ተጠቃሚ የማድረግ አቅም አላቸው፡፡ ይህም አነስተኛ አቅም ያላቸው ገበሬዎች የካፒታል፡ የቴክኖሎጂ፣ የእውቀትና የግብይት ቦታዎች አቅራቦት እንዲኖራቸው በማድረግ ነው፡፡ ከዚሁ ጐን ለጐን የላቀ ኢኮኖሚያዊ እምርታ እና የግብርና ምርታማነትን የመሳሰሉ ጠቀሜታዎችን ማግኘት ያስችላሉ፡፡ ቢሆንም እነዚህ ኘሮጅክቶች ብዙ ግዜ የአካባቢውን ነዋሪዎች መብቶቻቸውን እንዲያጡና መሬታቸውንና በመሰል የተፈጥሮ ሃብቶችም መ ጠቀም እ ንዳይችሉ በ ማድረግ ለ ተጐጂነት ይ ዳርጉዋቸዋል፡፡ እ ንደዚሁም በ ምግብ ዋስትናና በገጠር ነዋሪዎች እኗኗር ላይ ተፅእኖዎች አሳድረዋባቸዋል፡፡


ባመዛኙ በታዳጊ ሀገሮች ውስጥ በግብርና ስራ ላይ እንቬስትመንት የሚካሄደው ደካማ የመሬት ባለቤትነት አስተዳደር እና ድህነት በከፍተኛ ደረጃ በተንሰራፋባቸው አካባቢዎች ነው፡፡ በአገር አቀፍ የምግብ ዋስትና ማእቀፍ ውስጥ የመሬት፣ የአሳ ሀብት እና የደን ይዞታ መብት በኃላፊነት ማስተዳደርን የተመለከቱ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረቱ መመሪያዎች (መመሪያዎቹ) በተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ዋስትና ኮሚቴ በግንቦት 2004 ዓ .ም ይ ሁንታ አ ግኝተዋል፤ መ መሪያዎቹ የ ተፃፉትም እ ነዚህንና ሌ ሎች አ ገሮችም ጭ ምር የ መሬት ባለቤትነት አስተዳደራቸውን ለማሻሻል እንዲረዱ ታስቦ ነው፡፡ የመመሪያዎቹ አብይ አላማ የምግብ ዋስትና እጦትን እና ድህነትን መቀነስ ነው፡፡


መመሪያዎቹ በዋንኝነት ትኩርት ያደረጉት መንግስታት ላይ ቢሆንም ለግሉ ዘርፍም ሊተገበሩ የሚችሉ ጠቃሚ ቁም ነገሮችን በተጨማሪነት አካተዋል፡፡ ኢንቬስተሮች ኘሮጀክቶቻቸው ህጋዊ የመሬት ባለቤትነትንና ሰብዓዊ መብቶችን ለመተግበር እንዲችሉ ድጋፍ መስጠት ላይም ልዩ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ መመሪያዎቹ በከፍተኛ ደረጃ በመሬት፣ በደኖች እና በአሳ ሀብቶች ስራ ላይ ለሚውል ኢንቬስትመንት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ምርጥ የስራ ተሞክሮዎች ማሳያ ተደርገው ተወስደዋል፡፡ ከመመሪያዎቹ ጋር በሚጣጣም መልኩ እንቬስትመንቶቻቸውን የሚተገብሩ ክፍሎችን ሊየገጥም የሚችል አደጋን በመቀነስ ምክንያታዊና ተጐጂነትን ያገናዘበ ውጤት የማሳደግ እድል ይኖራቸዋል፡፡ እንደነዚህ ያሉ እንቬስትመንቶች ስኬታማ ሊሆኑ የሚችሉት እያንዳንዱ ኢንቬስተሩ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና መንግስት ተጠቃሚ መሆን ከቻሉ ብቻ ነው፡፡ ይህ ሙያዊ መምሪያ የሚሞክረው ኢንቬስተሮች የራሳቸውን ሚና በአግባቡ በመጫዎት ተፈላጊውን ውጤት ማግኘት በሚያስችሉዋቸው መንገዶች መመሪያዎቹን በተግባር መዋል እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡

Share on RLBI navigator
NO